አአእምሮን ማደስ አሁን ይግዙ · 3,499 ብር
ለሳይት መሐንዲሶች፣ ለፕሮጀክት ማኔጀሮችና ለኮንትራክተሮች

ሳይቱን በወረቀትና በግምት ሳይሆን በአንድ ሲስተም ይምሩ

የጊዜ ሰሌዳ (CPM)፣ Gantt፣ S-Curve፣ መጋዘን፣ የዕቃ ጥያቄ፣ የንዑስ ተቋራጭና የቀን ሠራተኞች ክፍያ — በአንድ Excel ፋይል። ከ104 ገጽ የአማርኛ መጽሐፍና ከ34 ዝግጁ የሳይት ቅጾች ጋር።

3,499ብር
አንድ ጊዜ ክፍያ · ከክፍያ በኋላ ወዲያውኑ ያውርዱ
አሁን ይግዙ →
ክፍያ፦ TelebirrCBE BirrM-PesaበYe-Buna በኩል
የሳይት መሐንዲስ ሙሉ የሥራ ኪት ሽፋን
104ገጽ የሳይት መሐንዲስ መጽሐፍ (PDF)
16የተያያዙ የExcel የሥራ ገጾች
15,000+ዝግጁ ቀመሮች — በራሳቸው ያሰላሉ
34ዝግጁ የሳይት ቅጾች (Word)
ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ

እነዚህን ጥያቄዎች ወዲያውኑ መመለስ ይችላሉ?

በተበታተኑ ወረቀቶችና ፋይሎች መልሱን ማግኘት ቀናት ይወስዳል። በዚህ ሲስተም ሁሉም በአንድ ዳሽቦርድ ላይ ነው።

ፕሮጀክቱ ከዕቅዱ ስንት በመቶ ወደኋላ ነው?
የትኞቹ ወሳኝ ሥራዎች ዘገዩ? ፕሮጀክቱ መቼ ያልቃል?
በመጋዘን ውስጥ የትኛው ዕቃ ከዝቅተኛው ክምችት በታች ወረደ?
የትኞቹ የዕቃ ጥያቄዎች ዘገዩ?
ለንዑስ ተቋራጮች ስንት ያልተከፈለ ገንዘብ አለ? መያዣው ስንት ነው?
የዚህ ወር የቀን ሠራተኞች ክፍያ ስንት ነው — ከትርፍ ሰዓቱ ጋር?
በ22 ሰከንድ

በኪቱ ውስጥ ያለውን ይመልከቱ

በቪዲዮው ውስጥ የሚያዩት ከእውነተኛው ፋይል የተወሰዱ ገጾችን ነው — ዳሽቦርድና S-Curve፣ Gantt እና የመጋዘን መዝገብ።

  • ሁሉም ገጾች በአማርኛ፣ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መመሪያ
  • ቢጫ ሴሎችን ብቻ ይሞላሉ፤ ቀሪውን ቀመሮቹ ያሰላሉ
  • በምሳሌ ፕሮጀክት ተሞልቶ ይመጣል — ሰርዘው የራስዎን ያስገባሉ
  • .xlsx ፋይል ነው፤ Macro የለውም
ዳሽቦርድ

የፕሮጀክቱ ሁኔታ በአንድ ገጽ

የሪፖርት ቀኑን በየሳምንቱ ሲቀይሩ ዳሽቦርዱ በራሱ ይታደሳል። አትመው በሳምንታዊ ስብሰባ ላይ ይጠቀሙበታል።

8.9% / 7.4%የታቀደ / የተከናወነ ሂደት
0.83SPI — የጊዜ አፈጻጸም
2የዘገዩ ወሳኝ ሥራዎች
1,540,440በመጋዘን ያለ የክምችት ዋጋ (ብር)
02_Site_Engineer_System.xlsx — ዳሽቦርድ
የሳይት ዳሽቦርድና S-Curve

ምሳሌ ፕሮጀክት፦ G+2 የመኖሪያ ሕንፃ · ጠቅላላ ዋጋ 24.33 ሚሊዮን ብር · ሳምንት 7። ቁጥሮቹ ምሳሌ ብቻ ናቸው። ምስሉን ለማስፋት ይጫኑ።

ከእውነተኛው ፋይል

ገጾቹን አንድ በአንድ ይመልከቱ

እነዚህ ምስሎች ከExcel ሲስተሙ የተወሰዱ ናቸው። ለማስፋት ምስሉን ይጫኑ።

የጊዜ ሰሌዳ
የጊዜ ሰሌዳ

እስከ 150 ሥራዎች — ቀናት፣ ቀኖች፣ ተንሳፋፊ ቀናትና ወሳኝ መስመር በራሳቸው ይሰላሉ

ብዛት ÷ (ምርታማነት × ቡድኖች) = ቀናት። እስከ 2 ቀዳሚ ሥራዎች ይገልጻሉ፤ መጀመሪያና መጨረሻ ቀኑ በራሱ ይወጣል።

Gantt
Gantt ቻርት

የጊዜ ሰሌዳው በሳምንታት (78 ሳምንት) በቀለም — ወሳኝ ሥራዎች በቀይ

ቢጫው አምድ የሪፖርት ሳምንቱን ያሳያል። መረጃው ከ"የጊዜ ሰሌዳ" ገጽ በራሱ ይመጣል።

የመጋዘን መዝገብ (Stock Ledger)
የመጋዘን መዝገብ

ገቢ (GRN)፣ ወጪ (SIV)፣ ተመላሽና ብክነት — እስከ 1,000 ግብይቶች

የዕቃው ቀሪ ክምችትና ዋጋ በራሱ ይሰላል፤ ከዝቅተኛው ክምችት በታች ሲወርድ "የዕቃ ዝርዝር" ገጽ ያስጠነቅቃል።

የዕቃ ጥያቄዎች (Material Requests)
የዕቃ ጥያቄዎች

የተጠየቀው፣ የደረሰውና የቀረው — የዘገዩ ጥያቄዎች ይለያሉ

የደረሰው መጠን ከመጋዘን መዝገቡ በራሱ ይነበባል።

ንዑስ ተቋራጮች — ውልና ማጠቃለያ
ንዑስ ተቋራጮች

የተረጋገጠ ሥራ፣ መያዣ፣ ቅድሚያ፣ የተከፈለና ቀሪ ክፍያ

ወርሃዊ የክፍያ ሰርተፊኬቶች ገጽ መያዣ፣ ቅድሚያ ተመላሽ፣ VAT እና 3% ቅድመ ግብር ተቀናሽ ያሰላል።

ሰዓት መቆጣጠሪያ
የቀን ሠራተኞች መገኘት

የ31 ቀን የመገኘት ሰንጠረዥና የትርፍ ሰዓት

1 = ሙሉ ቀን፣ 0.5 = ግማሽ ቀን። እስከ 150 የቀን ሠራተኞች።

የቀን ሠራተኞች የክፍያ ዝርዝር (Payroll)
የቀን ሠራተኞች ክፍያ

የክፍያ ዝርዝር ከፊርማ ቦታ ጋር — ትርፍ ሰዓት በአዋጅ 1156/2011 ተመን

ቅድሚያ ክፍያና የገቢ ግብር ተቀናሽ በራሳቸው ይቀነሳሉ።

የቁሳቁስ መጠን ማስያዎች
የቁሳቁስ ማስያዎች

ኮንክሪት፣ ብሎኬት፣ ልስን፣ ሴራሚክ፣ ቀለምና ብረት

ከታች ያለውን የኮንክሪት ማስያ አሁኑኑ ይሞክሩት — በፋይሉ ውስጥ ያለው ቀመር ይኸው ነው።

አሁኑኑ ይሞክሩት

የኮንክሪት ዕቃ ማስያ

በ"ማስያዎች" ገጽ ላይ ያለው ስሌት ነው። ቁጥሮቹን ይቀይሩ።

67ሲሚንቶ (50 ኪ.ግ. ከረጢት)
97,150የሲሚንቶ ወጪ (ብር)
3,326ሲሚንቶ (ኪ.ግ.)
1,663ውሃ (ሊትር፣ w/c 0.50)
4.62አሸዋ (m³)
9.24ጠጠር (m³)

ደረቅ መጠን = 1.54 × እርጥብ መጠን · ሲሚንቶ 1,440 ኪ.ግ./m³ · 50 ኪ.ግ. ከረጢት። 1,450 ብር ምሳሌ ዋጋ ነው፤ የአካባቢዎን ዋጋ ያስገቡ።

16ቱ የሥራ ገጾች

ሲስተሙ ምን ያደርጋል?

ሁሉም ገጾች እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው — አንድ ጊዜ ያስገቡት መረጃ በሌሎቹ ገጾች በራሱ ይጠቀማል።

1

ዳሽቦርድ

የታቀደ vs የተከናወነ %፣ SPI/CPI፣ የዘገዩና ወሳኝ ሥራዎች፣ የመጋዘን ማስጠንቀቂያዎች፣ የንዑስ ተቋራጭ ዕዳ፣ የሠራተኛ ወጪ

2

ፕሮጀክት

የፕሮጀክት መረጃ፣ የመጀመሪያ ቀን፣ በሳምንት የሥራ ቀናት፣ የሪፖርት ቀን፣ የትርፍ ሰዓት ተመኖች

3

የጊዜ ሰሌዳ (CPM)

እስከ 150 ሥራዎች፤ ቀናት፣ ቀኖች፣ ተንሳፋፊ ቀናትና ወሳኝ መስመር በራሳቸው

4

Gantt

78 ሳምንታት በቀለም፤ ወሳኝ ሥራዎች በቀይ

5

S-Curve እና የተገኘ ዋጋ

የታቀደ ድምር % በራሱ፤ PV፣ EV፣ SPI፣ CPI እና ገበታ

6

የዕቃ ዝርዝር

ዋና ዝርዝር፣ ዝቅተኛ ክምችት፣ የBOQ ፍጆታ፤ ቀሪ፣ ዋጋና ማስጠንቀቂያ

7

የመጋዘን መዝገብ

GRN፣ SIV፣ ተመላሽና ብክነት — እስከ 1,000 ግብይቶች

8

የዕቃ ጥያቄ

የዕቃ ጥያቄዎች (MR)፣ የደረሰው መጠን፣ የዘገዩ ጥያቄዎች ማስጠንቀቂያ

9

ንዑስ ተቋራጮች

ውልና ማጠቃለያ፦ የተረጋገጠ፣ መያዣ፣ ቅድሚያ፣ የተከፈለ፣ ቀሪ

10

የክፍያ ሰርተፊኬቶች

ወርሃዊ ክፍያ፦ መያዣ፣ ቅድሚያ ተመላሽ፣ ተቀናሽ፣ VAT፣ 3% ቅድመ ግብር

11

ሠራተኞች

የቀን ሠራተኞች ዝርዝር፣ ሙያና የቀን ክፍያ (እስከ 150)

12

ሰዓት መቆጣጠሪያ

የ31 ቀን መገኘትና የትርፍ ሰዓት

13

የቀን ሠራተኞች ክፍያ

የክፍያ ዝርዝር ከፊርማ ቦታ፣ ትርፍ ሰዓት በሕጉ ተመን፣ ቅድሚያና ግብር ተቀናሽ

14

ማስያዎች

ኮንክሪት፣ ብሎኬት፣ ልስን፣ ብረት፣ ሴራሚክና ቀለም

15

የምርታማነት መረጃ

ለጊዜ ሰሌዳው የሚያገለግሉ የተለመዱ የምርታማነት ግምቶች

16

ተመኖች

የደመወዝ ገቢ ግብርና የጡረታ ተመኖች

በየሳምንቱ የሚሠሩት 6 ደረጃዎች ብቻ

"ፕሮጀክት" ገጽ ላይ የሪፖርት ቀኑን ይቀይሩ
"የጊዜ ሰሌዳ" ላይ የእያንዳንዱን ሥራ የተከናወነ % ያዘምኑ
"S-Curve" ላይ የሳምንቱን የተከናወነ % እና የወጪ ድምር ያስገቡ
የሳምንቱን GRN እና SIV በመጋዘን መዝገብ ያስገቡ
የቀን ሠራተኞችን መገኘት በየቀኑ ይሙሉ
ዳሽቦርዱን አትመው ለሳምንታዊ ስብሰባ ይጠቀሙ
34 ዝግጁ ቅጾች (Word)

ለሳይቱ የሚያስፈልጉ ቅጾች በሙሉ

የድርጅትዎን ስምና ሎጎ አስገብተው ወዲያውኑ ያትሟቸዋል።

1ዕለታዊ የሳይት ሪፖርት2ሳምንታዊ የሂደት ሪፖርት3የወርሃዊ ሪፖርት ማውጫ4የሳይት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ5የደብዳቤ መዝገብ6የቃል መመሪያ ማረጋገጫ7RFI8የዕቃ ጥያቄ9የዕቃ መቀበያ (GRN)10የዕቃ ማውጫ (SIV)11የዕቃ ተመላሽ12ቢን ካርድ13የመጋዘን ቆጠራ ሉህ14የዕቃ ጥራት ፍተሻ15የፍተሻ ጥያቄ16Pour Card17የኮንክሪት ኪዩብ መዝገብ18የብረት ሥራ ፍተሻ19NCR20Snag List21የቀን ሠራተኛ ምዝገባ22የሳምንት መገኘት ሉህ23የቀን ሠራተኞች ክፍያ24የትርፍ ሰዓት ፈቃድ25የንዑስ ተቋራጭ ውል26የንዑስ ተቋራጭ ልኬት27የንዑስ ተቋራጭ ክፍያ ሰርተፊኬት28የመሣሪያ ዕለታዊ መዝገብ29የነዳጅ መስጫ መዝገብ30የደህንነት ውይይት መዝገብ31PPE መረከቢያ32የአደጋ ሪፖርት33ሳምንታዊ የደህንነት ፍተሻ34የጎብኚዎች መዝገብ
የመጽሐፉ ሽፋን ምዕራፍ 7 — የሥራ ክፍፍል ዕለታዊ የሳይት ሪፖርት ቅጽ

104 ገጽ መጽሐፍ — 37 ምዕራፎች

እያንዳንዱ ምዕራፍ ከExcel ሲስተሙና ከቅጾቹ ጋር የተገናኘ ነው። ከምዕራፎቹ ጥቂቶቹ፦

  • የመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት፦ ሳይትን ማቋቋም
  • የወሳኝ መስመር ዘዴ (CPM) ደረጃ በደረጃ
  • S-Curve እና የተገኘ ዋጋ (Earned Value)
  • መዘግየት፣ ማሳወቂያና የጊዜ ማራዘሚያ
  • የመጋዘን አያያዝና ብክነት ቁጥጥር
  • የቀን ሠራተኞችና የንዑስ ተቋራጮች አስተዳደር
  • ልኬትና የክፍያ ጥያቄ (IPC)
  • የዋጋ ትንተና (Rate Analysis) በምሳሌ
  • ኮንክሪት፦ ከቅይጥ እስከ ኪዩሪንግ
  • የተለመዱ የሳይት ጉድለቶች፦ ምክንያትና መፍትሔ
  • የ12 ሳምንታት የደህንነት ውይይቶች
  • ርክክብና የፕሮጀክት መዝጊያ
ለማን ነው?

ሳይት ለሚመራ ሁሉ

👷
የሳይት መሐንዲሶች
📋
የፕሮጀክት ማኔጀሮች
🏗️
ኮንትራክተሮች
🦺
ፎርማኖች
የሚያገኙት

3 ፋይሎች — በአንድ ZIP

  • PDF
    የሳይት መሐንዲስ መጽሐፍ — 104 ገጽ37 ምዕራፎች፣ በምሳሌ ፕሮጀክት የተብራራ
  • XLSX
    የሳይት ሲስተም Excel — 16 የሥራ ገጾች + መመሪያበምሳሌ ፕሮጀክት ተሞልቶ · ከ15,000 በላይ ቀመሮች · Macro የለውም
  • DOCX
    34 ዝግጁ የሳይት ቅጾችሪፖርቶች፣ መጋዘን፣ ጥራት፣ ክፍያ፣ ደህንነት
3,499ብር
አንድ ጊዜ ክፍያ · ወርሃዊ ክፍያ የለውም
አሁን ይግዙ →
TelebirrCBE BirrM-Pesa
በሦስት ደረጃ

እንዴት ይገዛሉ?

1

"አሁን ይግዙ" ይጫኑ

ወደ Ye-Buna የምርቱ ገጽ ይወስድዎታል።

2

3,499 ብር ይክፈሉ

በTelebirr፣ በCBE Birr ወይም በM-Pesa።

3

ወዲያውኑ ያውርዱ

ክፍያው እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል — PDF + Excel + Word በአንድ ZIP።

ጥያቄዎች

በብዛት የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ፋይሉ Macro አለው?

የለውም። ፋይሉ .xlsx ነው — ሁሉም ስሌቶች በተለመዱ የExcel ቀመሮች ይሰራሉ።

ምን ዓይነት Excel ያስፈልገኛል?

Microsoft Excel 2016፣ 2019፣ 2021 ወይም Microsoft 365 ይመከራል። መረጃ ለማስገባት ኮምፒውተር የተሻለ ነው።

በስልክ ይሰራል?

በስልክዎ በExcel መተግበሪያ ገጾቹን ማየትና ማንበብ ይችላሉ፤ መጽሐፉና ቅጾቹም በስልክ ይከፈታሉ። ሙሉ የጊዜ ሰሌዳ ለመሙላት ግን ኮምፒውተር ይመከራል።

ለራሴ ፕሮጀክት እንዴት እጠቀምበታለሁ?

ፋይሉ በምሳሌ ፕሮጀክት (G+2 የመኖሪያ ሕንፃ) ተሞልቶ ይመጣል። የምሳሌውን ቁጥሮች ሰርዘው በቢጫ ሴሎቹ ላይ የራስዎን ፕሮጀክት ያስገባሉ። በ"መመሪያ" ገጽና በመጽሐፉ ምዕራፍ 4–5 ላይ ደረጃ በደረጃ ተብራርቷል።

ቀመሮቹ እንዳይበላሹ ምን ላድርግ?

ሴሎቹ በቀለም ተለይተዋል፦ ቢጫ = እርስዎ የሚሞሉት፣ ሰማያዊ = የሕጉ ተመን፣ ጥቁር = በቀመር የሚሰላ። ቢጫ ሴሎችን ብቻ ይሙሉ። ለእያንዳንዱ አዲስ ፕሮጀክት የፋይሉን ቅጂ ይጠቀሙ።

ለብዙ ፕሮጀክቶች መጠቀም እችላለሁ?

አዎ። ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት የፋይሉን ቅጂ አድርገው ይጠቀማሉ — ተጨማሪ ክፍያ የለውም።

ከከፈልኩ በኋላ ፋይሉን እንዴት አገኛለሁ?

ክፍያዎ በYe-Buna እንደተጠናቀቀ የማውረጃ ሊንክ ይደርስዎታል። ZIP ፋይሉን አውርደው ይከፍቱታል።

ክፍያ ቢቋረጥብኝ ወይም ፋይሉ ባይደርሰኝስ?

ገንዘብዎ ተቀንሶ ፋይሉ ካልደረሰዎት የክፍያውን ማረጋገጫ (ደረሰኝ ወይም የSMS መልዕክት) ይዘው ያግኙን — ፋይሉን እንልክልዎታለን።

ማሳሰቢያ፦ በፋይሉና በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት ቁጥሮች ምሳሌ ብቻ ናቸው። የምርታማነትና የቁሳቁስ መጠኖች የተለመዱ የመስክ ግምቶች ስለሆኑ ለፕሮጀክትዎ ያስተካክሏቸው። ይህ ኪት ለሥራ ማቀላጠፊያ የተዘጋጀ ነው፤ የሕግ ወይም የሙያ ምክር አይደለም።

የሚቀጥለውን ሳምንታዊ ስብሰባ በዳሽቦርድ ይምሩ

104 ገጽ መጽሐፍ + Excel ሲስተም + 34 ቅጾች — 3,499 ብር፣ አንድ ጊዜ ክፍያ።

አሁን ይግዙ →
3,499 ብርአንድ ጊዜ ክፍያ
አሁን ይግዙ →